በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተቋም ግንባታ
በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ወጥነት ያለው፣ የተቀናጀ፣ ተለኪ እንዲሁም ብክነትን ያስወገዱ እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩት የሚያስችል የሚያስችል የአሠራር ሥርዐትን መገንባት
በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ወጥነት ያለው፣ የተቀናጀ፣ ተለኪ እንዲሁም ብክነትን ያስወገዱ እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩት የሚያስችል የሚያስችል የአሠራር ሥርዐትን መገንባት
ተቋማት ዓላማ እና ርእያቸውን በማስቀመጥ ለትግበራውም ልዩ ልዩ የረዥም ጊዜ እና የአጭር ጊዜ ስልቶችን በመቅረጽ ይንቀሳቀሳሉ። የአላማቸው ስኬት የሚወሰነው በፍላጎት፣ ተነሳሽነት፣ እቅድ ወዘተ . . . ብቻ ሳይሆን በውጤታማ፣ ብክነትን ያስወገደ እና ተለኪ አፈጻጸማቸውም ጭርም ነው። በመሆኑም ተቋማት በተመሰከረላቸው መልካም የአሰራር መሠረት /Best Practices/ ላይ የተገነባ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተቋም አደረጃጀት እና የአመራር ስርዓት ሊኖራቸው ግድ ይላል።
አጥቢያ ዶት ኮም በዘርፉ የብዙ አመት ልምድ ያላቸውን ባለሞያዎችዋን በመጠቀም የሚከተሉትን ፭ ደረጃዎች ያሉትን ሒደት አበልጽጋለች። እነሱም፦
፩. ፍተሻ/ጥናት ማድረግ
፪. መሠረታዊ ጉዳዮችን ማጥራት
፫. ስልት እና ፖሊሰ ዝግጅት
፬. ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን መቅረጽ እና መተግበር
፭. የውጤታማ ተቋም ግንባታ ባህልን መፍጠር