የኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛወረ

ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.
+ + +
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የሚገኘው ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከዚህ ቀደም በፈቃደኛ አገልጋዮች ሲያስተዳደር የነበረውን የድረገጽ እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛውሯል። የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ተስፋሚካኤል መኮንን ይህንን ለማድረግ ያስፈለገው በሁለት ዋና ምክንያቶች እንደሆነ ገልጸዋል። እነሱም፦
  1. ድረገጹን ሲያስተዳደሩ የነበሩ ፈቃደኛ አገልጋዮች ባጋጠማቸው የስራ ጫና እና ተያያዥ ምክንያቶች ድረገጹ የሚያስፈልገውን የእለት ተእለት ክትትል ለማድረግ ባለመቻሉ እና የአገልግሎት መቋረጥ በማጋጠሙ እና
  2. በቀጣይ ከድረገጽ ባለፈ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ እና የማዘመን ስልታዊ አቅጣጫን ደብሩ በማስቀመጡ ነው ብለዋል።
አጥቢያ ዶት ኮም የደብሩን ድረገጽ በጥንቃቄ በነበረበት መልኩ ያለምንም የአገልግሎት መቋረጥ (zero downtime) ወደ አጥቢያ ዶት ኮም ሰርቨሮች ያሸጋገረ ሲሆን በቀጣይ የገጽታ እና ሌሎች ማሻሻያዎችን በማድረግ የድረገጹን ተደራሽነት ለማሳደግ ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።

ፎቶ፦ ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል መኮንን