አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ለሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክ የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተጠናቀቀ

ለሰባት ተከታታይ ሳምንታት በበይነ መረብ የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና በትናንትናው እለት ተጠናቅቋል። በስልጠናው የተለያዩ መሰረታዊ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን ስልጠናው በገለጻ፣ ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተደገፈ እንደነበር ታውቋል። የተሸፈኑት ዋና ዋና አርእስት፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ፣ ባህል እና የለውጥ አመራር፣ ባህል እና የለውጥ አመራር፣ ውጤታማ ተግባቦት፣ ውጤታማ ስብሰባ፣ በእቅድ መመራት እና የአሰራር መመሪያ ዝግጅት እንደሆኑ ታውቋል።

በመርሐግብሩ ማጠቃለያ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀትጉኃን ቀሲስ ብርሃኑ ደሳለኝ ይህ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ እድለኛ ነው። ውጤታማ ሥራን ለመስራት እና የበለጠ ለማገልገል የሚረዱ ክህሎቶችን ያስተዋወቀ ስልጠና አግኝቷል ብለዋል። እንዲሁም ለመርሐግብሩ ዝግጅት ቁልፍ የማስተባበር ስራን የሰሩት ቀሲስ ተመስገን ቅጣው ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኟቸውን እውቀቶች በስራ ለመተግበር ሶስት ነገሮች ፡- ቁርጥ ውሳኔ፣ ትግበራ እና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መሻገር፣ ወደቀደመ አሰራሮች ላለመመለስ መታገል ያስፈልጋል ብለዋል

በመርሐግብሩ መዝጊያ ላይ አጥቢያ ዶት ኮም የስልጠናውን ቀጣይ ትግበራ የማገዝ እና የመከታተል ስራን የሚሰራ ሲሆን በቀጣይነትም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ መርሐግብሮች ቀርጾ እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/favicon-1.png 110 87 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2024-04-04 14:31:152024-04-04 14:35:55ለሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክ የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተጠናቀቀ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ለትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሰጠ Link to: የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ለትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሰጠ የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ለትሮንዳሔም ምሥራቀ... Link to: ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰጠ Link to: ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰጠ ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በኦስሎ ማህደረ ስብሐት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top