አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛወረ

ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.
+ + +
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የሚገኘው ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከዚህ ቀደም በፈቃደኛ አገልጋዮች ሲያስተዳደር የነበረውን የድረገጽ እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛውሯል። የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ተስፋሚካኤል መኮንን ይህንን ለማድረግ ያስፈለገው በሁለት ዋና ምክንያቶች እንደሆነ ገልጸዋል። እነሱም፦
  1. ድረገጹን ሲያስተዳደሩ የነበሩ ፈቃደኛ አገልጋዮች ባጋጠማቸው የስራ ጫና እና ተያያዥ ምክንያቶች ድረገጹ የሚያስፈልገውን የእለት ተእለት ክትትል ለማድረግ ባለመቻሉ እና የአገልግሎት መቋረጥ በማጋጠሙ እና
  2. በቀጣይ ከድረገጽ ባለፈ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ እና የማዘመን ስልታዊ አቅጣጫን ደብሩ በማስቀመጡ ነው ብለዋል።
አጥቢያ ዶት ኮም የደብሩን ድረገጽ በጥንቃቄ በነበረበት መልኩ ያለምንም የአገልግሎት መቋረጥ (zero downtime) ወደ አጥቢያ ዶት ኮም ሰርቨሮች ያሸጋገረ ሲሆን በቀጣይ የገጽታ እና ሌሎች ማሻሻያዎችን በማድረግ የድረገጹን ተደራሽነት ለማሳደግ ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።

ፎቶ፦ ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል መኮንን
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/kesis-tesfameichael-cover.jpg 413 400 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2023-10-31 20:15:232023-10-31 20:36:30የኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛወረ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ Link to: የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች... Link to: የስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ድረገጽ ተሻሽሎ ቀረበ Link to: የስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ድረገጽ ተሻሽሎ ቀረበ የስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top