ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሚያመጣቸውን መልካም አጋጣሚዎች ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፈጸሚያነት ለማዋል እንዲሁም ተግዳሮቶችን ለመቋቋም አጽንዖት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
አጥቢያዎች ከምእመናን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማዘመን በሁሉም ዘርፎች የተቀላጠፈ አገልግሎትን ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ ይህ መተግበሪያ ተዘጋጅቶልዎታል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ ውጤታማ የሆነ ተቋም ግንባታን ለመተግበር የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የመነሻ ጥናት፣ የግብአት ዝግጅት፣ የአተገባበር ስልት እና ቀጣይ ሞያዊ ድጋፍ ሊያስፈልግ ይችላል።
ስለአጥቢያ ዶት ኮም፣ ስለአገልግሎቶቻችን እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥቆማወይም አስተያየትዎን ያካፍሉን። እርዳታ ቢያስፈልግዎም በፍጥነት ያሳውቁን።
የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ
በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት የተሰራው የዚህ አመት (2015) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠናቀቀ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ድረ-ገጽ ተለቀቀ
የሀገረ ስብከቱ ድረገጽ በብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ቡራኬ ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ስራ ጀምሯል።
የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጀመረ
አጥቢያ ዶት ኮም የዚህን ዓመት /2015 ዓ.ም./ የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ዝግጅት ስራን ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ይፋዊ ድረ-ገጽ ተለቀቀ !
በአጥቢያ ዶት ኮም የተስራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ይፋዊ ድረገጽ የ2015 ዓ.ም. ጥምቅት በዓልን ምክንያት በማድረግ ተለቀቀ።
የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ተሰጠ
አጥቢያ ዶት ኮም በቅርቡ ሰርቶ ያስረከበውን የስዊድን፣ ስካንዲናቭያና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ድረገጽ የማስተዳደር ሥልጠና ሀገረ ስብከቱ የአይ.ሲ.ቲ. /Information Communication Technology/ ክፍል አባላት ትናንት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ተሰጠ