አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሰጠ

በኖርዌይ ትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለስድስት ተከታታይ ሳምንታት በበይነ መረብ የተሰጠው የውጤታማ ስራ አመራር ስልጠና በትናንትናው እለት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በስልጠናው የተካተቱ የይዘት አርእስት የኢ/ኦ/ተ/ቤ፣ ባህል እና የለውጥ አመራር፣ ውጤታማ ተግባቦት፣ ውጤታማ ስብሰባ፣ በእቅድ መመራት፣ የአሰራር መመሪያ ዝግጅት እና አገልግሎት ሲሆኑ ስልጠናው በአጥቢያ ዶት ኮም ባለሞያዎች በሚሰጥ ገለጻ፣ ሰልጣኞችን ያሳተፈ ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ እንደነበረ ታውቋል።

የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ አባ ቀለመወርቅ አቡኔ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ የገለጹ ሲሆን ስልጠናው ብዙ ጉዳዮችን የሸፈነ እንደመሆኑ ወደ ትግበራ በመቀየር የሚጨበጥ ውጤቶችን ማስመግዘብ ይገባናል ብለዋል።

አጥቢያ ዶት ኮም በቀጣይ የክፍሎች አሰራር መመሪያዎች ዝግጅት እንዲሁም አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ፕሮጀክቶችን ከደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ጋር በመሆን የሚተገብር መሆኑም ተገልጿል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/aba-kelemework-300.jpg 300 300 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2024-11-02 10:27:572024-11-02 10:46:12ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተሰጠ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል ውስጣዊ አሠራር መመሪያ በሸገር ከተማ ሃገረ ስብከት ደ/ኃ/ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ፍሬ ስብሐት Link to: የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል ውስጣዊ አሠራር መመሪያ በሸገር ከተማ ሃገረ ስብከት ደ/ኃ/ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ፍሬ ስብሐት የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል ውስጣዊ አሠራር መመሪያ... Link to: “Atbiya App – አጥቢያ” የአንድሮይድ መተግበሪያ ተለቀቀ Link to: “Atbiya App – አጥቢያ” የአንድሮይድ መተግበሪያ ተለቀቀ “Atbiya App – አጥቢያ” የአንድሮይድ መተግበሪያ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top