አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰጠ

በኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ለአምስት ተከታታይ ሳምንታት በበይነ መረብ የተሰጠው የውጤታማ ስራ አመራር ስልጠና በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በስልጠናው የተካተቱ የይዘት አርእስት የኢ/ኦ/ተ/ቤ፣ ባህል እና የለውጥ አመራር፣ ውጤታማ ተግባቦት፣ ውጤታማ ስብሰባ፣ በእቅድ መመራት፣ የአሰራር መመሪያ ዝግጅት እና ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ሲሆኑ ስልጠናው በአጥቢያ ዶት ኮም ባለሞያዎች በሚሰጥ ገለጻ፣ ሰልጣኞችን ያሳተፈ ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ እንደነበረ ታውቋል።

የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል መኮንን በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። ስልጠናው ብዙ ክህሎቶችን ያስጨበጠ ሲሆን በቀጣይም ወደ ትግበራ በመቀየር የአሰራር ማሻሻያዎችን ማስመግዘብ ይገባናል ብለዋል። በተጨማሪም በጅማሮ ላይ ያለው የደብሩ ስልታዊ እቅድ ዝግጅት ከአጥቢያ ዶት ኮም በሚደረገው ሞያዊ ድጋፍ የደብሩን ማኅበረሰብ አሳታፊ በሆነ መልኩ በልጽጎ ስራ ላይ እንዲውል እንሰራለን ብለዋል።

አጥቢያ ዶት ኮም በቀጣይ የክፍሎች አሰራር መመሪያዎች ዝግጅት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ክፍልና የማዋቀር እና ስራ የማስጀመር ፕሮጀክቶችን ከደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ጋር በመሆን የሚተገብር መሆኑም ተገልጿል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/kesis-tesfameichael-cover.jpg 413 400 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2024-04-26 19:48:332024-04-26 20:00:35ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በኦስሎ ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተሰጠ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: ለሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክ የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተጠናቀቀ Link to: ለሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ኃይማኖት ቤ/ክ የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተጠናቀቀ ለሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ኃይማኖት... Link to: የማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ Link to: የማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ የማኅበረ ቅዱሳን የ2016 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top