አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ድረ ገጽ ተለቀቀ

 

በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ድረ ገጽ ተለቀቀ።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፣ አገልግሎቱን ለማሳለጥ የሚያስችል መምሪያው ፫ኛውን ሀገር አቀፍ የስብከተ ወንጌል ቀን በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እያከበረ ባለበት በዚህ የታሪካዊ ጉባኤ ላይ፣ www.eotceam.org የተሰኘውን አዲስ ድረ ገጽ በይፋ ሥራ መጀመሩ ተበሥሯል።
​ይኽ ድረ ገጽ ከሌሎች መሰል ድረ ገጾች ለየት የሚያደርገው የአገልግሎት አድማሱ ባለብዙ ቋንቋ አገልግሎት (Multilingual Support) ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፤ በትግርኛ እና በእንግሊዝኛ፣ቋንቋዎች የተዘጋጀ መኾኑ ተመላክቷል።
ይኽም ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥም ኾነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ ምእመናን በቋንቋቸው ትምህርተ ወንጌልን ለማድረስ የያዘችውን ስትራቴጂያዊ ግብ የሚያሳካ መኾኑ ተገልጿል። ድረ ገጹ በዋናነት ​​የምእመናንን ዕውቀት ለማሳደግና ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ መሠረታዊና ወቅታዊ ትምህርቶች እንዱኹም ዜናዎች፤ የቤተክርስቲያንን አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ የመምሪያውን የሥራ ክንውንና ወቅታዊ ክስተቶችን ለሕዝብ ተደራሽ የሚያደርግ መኾኑ ተነግሯል።
(ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ገጽ)
ድረገጹን ይመልከቱ
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/eotceam.org-cover.png 401 400 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2026-04-27 15:22:012026-04-27 15:42:54በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ድረ ገጽ ተለቀቀ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: በኢ/ኦ/ተ/ቤ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ድረ ገጽ ተለቀቀ Link to: በኢ/ኦ/ተ/ቤ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ድረ ገጽ ተለቀቀ በኢ/ኦ/ተ/ቤ የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top