የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት የተሰራው የዚህ አመት (2015) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በፕሮጀክቱ ሒደት ልዩ ልዩ የሲስተም ማሻሻያ ስራዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የተካሔዱ ሲሆን የዚህ አመት ዲጅታል መጽሔት በይዘት እና በጥራት ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑ ታውቋል። ዲጅታል የምረቃ መጽሔቱ ለተመራቂዎች ከዛሬ ጀምሮ በስርጭት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያው የማስተዋወቂያ መርሐግብር እንደሚያዘጋጅ ታውቋል።።

አጥቢያ ዶት ኮም ለፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት አስተባባሪዎች (በሁሉም እርከን ላይ የሚገኙ) ከፍ ያለ ምስጋናን ያቀርባል።

የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው የዚህ አመት (2014) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በፕሮጀክቱ ሒደት ልዩ ልዩ የሲስተም ማሻሻያ ስራዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የተካሔዱ ሲሆን የዚህ አመት ዲጅታል መጽሔት በይዘት እና በጥራት ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑ ታውቋል። ዲጅታል የምረቃ መጽሔቱ ለተመራቂዎች ከዛሬ ጀምሮ በስርጭት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያው ሙሉ የትግበራ አቅጣጫውን በተዘጋጀው መተግበሪያ እንደሚያደርግ ታውቋል።

አጥቢያ ዶት ኮም ለፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት አስተባባሪዎች (በሁሉም እርከን ላይ የሚገኙ) ከፍ ያለ ምስጋናን ያቀርባል።

ውጤታማ እቅድ ዝግጅት በሚል ርዕስ ስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ

ትናንት ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. “ውጤታማ እቅድ ዝግጅት” በሚል ርዕስ በአጥቢያ ዶት ኮም አስተባባሪነት በአለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤት አንድነት የስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ።

በመርሐግብሩ 35 ተሳታፊዎች የታደሙ ሲሆን በአውደጥናት መልክ በውይይት እና ገለጻዎች በታጀበ መልኩ ተካሒዷል። በስልጠናው የተሸፈኑ አንኳር ነጥቦች፦
1. የእቅድ ምንነት እና አስፈላጊነት
2. በእቅድ ዝግጅት ዙሪያ ያሉ ጽንሰ ሐሳቦች
3. ወደ መሬት ለማውረድ የሚያግዝ የትግበራ ሒደት እና ተያያዥ ቅጾች

መርሐግብሩ መነሻ ግንዛቤን መፍጠር የቻለ ሲሆን በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ አቅጣጫዎችንም ጠቋሚ ሆኗል። በተቋም ግንባታ ዙሪያ የሚሰጡ ስልጠናዎች እና የምክክር መርሐግብሮቹ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጀመረ

አጥቢያ ዶት ኮም የዚህን ዓመት /2014 ዓ.ም./ የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራን ዓርብ ሚያዚያ 7/2014 ዓ.ም. በበይነ መረብ በተካሄደ የፕሮጀከት ማስጀመሪያ መርሐግብር ጀምሯል።

የትግበራ ፕሮጀክቱ በ3 ግብረ ኃይሎች የተከፈለ ሲሆን በትግበራው ግዜ ሰሌዳ መሰረትም ፕሮጀከቱ ሰኔ 30 ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ማስገባት፣ ዲጅታል መጽሔቱን የማዘጋጀት እና ተደራሽ የማድረግ ዋና ዋና ግቦችን ይዞ የሚሰራ ይሆናል። በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብሩ የአጥቢያ ዶት ኮም ባለሞያዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አይ.ሲ.ቲ. ክፍል ተወካዮች፣ የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ እንዲሁም ሌሎች የማኅበረ ቅዱሳን ስራ አስፈጻሚ ተወካዮች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።