ውጤታማ እቅድ ዝግጅት በሚል ርዕስ ስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ

ትናንት ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. “ውጤታማ እቅድ ዝግጅት” በሚል ርዕስ በአጥቢያ ዶት ኮም አስተባባሪነት በአለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤት አንድነት የስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ።

በመርሐግብሩ 35 ተሳታፊዎች የታደሙ ሲሆን በአውደጥናት መልክ በውይይት እና ገለጻዎች በታጀበ መልኩ ተካሒዷል። በስልጠናው የተሸፈኑ አንኳር ነጥቦች፦
1. የእቅድ ምንነት እና አስፈላጊነት
2. በእቅድ ዝግጅት ዙሪያ ያሉ ጽንሰ ሐሳቦች
3. ወደ መሬት ለማውረድ የሚያግዝ የትግበራ ሒደት እና ተያያዥ ቅጾች

መርሐግብሩ መነሻ ግንዛቤን መፍጠር የቻለ ሲሆን በቀጣይ ሊሰራባቸው የሚገቡ አቅጣጫዎችንም ጠቋሚ ሆኗል። በተቋም ግንባታ ዙሪያ የሚሰጡ ስልጠናዎች እና የምክክር መርሐግብሮቹ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጀመረ

አጥቢያ ዶት ኮም የዚህን ዓመት /2014 ዓ.ም./ የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራን ዓርብ ሚያዚያ 7/2014 ዓ.ም. በበይነ መረብ በተካሄደ የፕሮጀከት ማስጀመሪያ መርሐግብር ጀምሯል።

የትግበራ ፕሮጀክቱ በ3 ግብረ ኃይሎች የተከፈለ ሲሆን በትግበራው ግዜ ሰሌዳ መሰረትም ፕሮጀከቱ ሰኔ 30 ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ማስገባት፣ ዲጅታል መጽሔቱን የማዘጋጀት እና ተደራሽ የማድረግ ዋና ዋና ግቦችን ይዞ የሚሰራ ይሆናል። በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብሩ የአጥቢያ ዶት ኮም ባለሞያዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አይ.ሲ.ቲ. ክፍል ተወካዮች፣ የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ እንዲሁም ሌሎች የማኅበረ ቅዱሳን ስራ አስፈጻሚ ተወካዮች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።