ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሚያመጣቸውን መልካም አጋጣሚዎች ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፈጸሚያነት ለማዋል እንዲሁም ተግዳሮቶችን ለመቋቋም አጽንዖት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
አጥቢያዎች ከምእመናን ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማዘመን በሁሉም ዘርፎች የተቀላጠፈ አገልግሎትን ለመስጠት እንዲያስችል ታልሞ ይህ መተግበሪያ ተዘጋጅቶልዎታል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ ውጤታማ የሆነ ተቋም ግንባታን ለመተግበር የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የመነሻ ጥናት፣ የግብአት ዝግጅት፣ የአተገባበር ስልት እና ቀጣይ ሞያዊ ድጋፍ ሊያስፈልግ ይችላል።
ስለአጥቢያ ዶት ኮም፣ ስለአገልግሎቶቻችን እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥቆማወይም አስተያየትዎን ያካፍሉን። እርዳታ ቢያስፈልግዎም በፍጥነት ያሳውቁን።
የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ተሰጠ
አጥቢያ ዶት ኮም በቅርቡ ሰርቶ ያስረከበውን የስዊድን፣ ስካንዲናቭያና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ድረገጽ የማስተዳደር ሥልጠና ሀገረ ስብከቱ የአይ.ሲ.ቲ. /Information Communication Technology/ ክፍል አባላት ትናንት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ተሰጠ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ የስዊድን እና ስካንዲናቭያ ሀገሮች አህጉረ ስብከት ድረገጽ ተለቀቀ
በአጥቢያ ዶት ኮም አበልጻጊነት የተሰራው የአህጉረ ስብከቱ ድረገጽ የመነሻ መረጃዎችን በመያዝ በመስቀል እለት መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ ውሏል
በኤ/ኦ/ተ/ቤ የስካንዲናቭያ እና ፊንላንድ ሀገረስብከት ድረገጽ ተሻሽሎ ተለቀቀ
በአጥቢያ ዶት ኮም አበልጻጊነት የተሰራው የሀገረስብከቱ ድረገጽ ትልቅ የሆነ የቴክኖሎጂ እና የገጽታ ማሻሻል ተደርጎበት ለተጠቃሚዎች ቀረበ
የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ
በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው የ2014 ዓ.ም. የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተጠናቀቀ
ውጤታማ እቅድ ዝግጅት በሚል ርዕስ ስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ
ትናንት ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. “ውጤታማ እቅድ ዝግጅት” በሚል ርዕስ በአጥቢያ ዶት ኮም አስተባባሪነት በአለም አቀፍ የሰንበት ት/ቤት አንድነት የስልጠና እና የምክክር መርሐግብር ተካሔደ።