በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃማኖት ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክሳዊ ሥራ አመራር እና ተግባቦት ስልጠና ተሰጠ
ሥልጠናው ኦርቶዶክሳዊ ሥራ አመራር እና ተግባቦት በሚሉ አርእስት በሁለት መርሐግብር የተካሔደ ሲሆን በገለጻ እና ሰፊ ውይይት የታገዘ እንደነበር ተገልጿል። ይህ ሥልጠና በቀጣይ ደብሩ ለሚያደርጋቸው የሥራ አመራር አሠራር ማሻሻያዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተነሳሽነት መፍጠር ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በስልጠናውም የደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት እና የክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።
አጥቢያ ዶት ኮም ደብሩ የጀመረውን መልካም እንቅስቃሴዎች ከግብ እንዲያደርስ የሚያስፈልገውን ድጋፍ በማድረግ በቀጣይነት አብሮ እንደሚሰራ ተገልጿል።

