ውጤታማ የስራ አመራር ስልጠና በሸገር ከተማ ሃገረ ስብከት ደ/ኃ/ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ፍሬ ስብሐት ሰ/ት ቤት ተሰጠ
በሸገር ከተማ ሃገረ ስብከት የለኩ ደ/ኃ/ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ፍሬ ስብሐት ሰ/ት ቤት ለስድስት ተከታታይ ሳምንታት የተሰጠው የውጤታማ ስራ አመራር ስልጠና እሑድ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። ስልጠናው የተሰጠው በበይነ መረብ (ኦንላይን) ሲሆን ተሳታፊዎች በገለጻ፣ ውይይት እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ባካተተ መልኩ ስልጠናውን ተከታትለዋል።
በስልጠናው የፍጻሜ መርሐግብር ላይ የሰንበት ት/ቤቱ ሰብሳቢ አርክቴክት ነብዩ አጥቢያ ዶትኮምን ያመሰገኑ ሲሆን ሰልጣኞች የቀሰሙትን ልምድ በስራ ላይ በማዋል የሚታይ፣ የሚለካ ለውጥ ለማምጣት መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አጥቢያ ዶት ኮም ከሰንበት ት/ቤቱ ጋር በቀጣይነት የሥራ መመሪያዎች ዝግጅት እና አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።