የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው የዚህ አመት (2014) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በፕሮጀክቱ ሒደት ልዩ ልዩ የሲስተም ማሻሻያ ስራዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የተካሔዱ ሲሆን የዚህ አመት ዲጅታል መጽሔት በይዘት እና በጥራት ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑ ታውቋል። ዲጅታል የምረቃ መጽሔቱ ለተመራቂዎች ከዛሬ ጀምሮ በስርጭት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያው ሙሉ የትግበራ አቅጣጫውን በተዘጋጀው መተግበሪያ እንደሚያደርግ ታውቋል።

አጥቢያ ዶት ኮም ለፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት አስተባባሪዎች (በሁሉም እርከን ላይ የሚገኙ) ከፍ ያለ ምስጋናን ያቀርባል።