የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ድረ ገጽ ተለቀቀ

 

በአጥቢያ ዶት ኮም የተስራው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ድረገጽ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም.  ተለቀቀ።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ይፋ ያደረገው ይህ ዲጂታል መድረክ፤ ከመደበኛ የዜና ማሰራጫነት ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መረጃዎች በአንድ ማዕከል አደራጅቶ የያዘ “ዲጂታል መረጃ ማዕከል” ሆኖ ያገለግላል፡፡
ይህ አዲስ ድረ-ገጽ ከመንበረ ፓትርያርክ የሚወጡ ይፋዊ መግለጫዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ለምዕመናን የሚደርሱበት አማራጭም ይሆናል ተብሏል፡፡