አጥቢያ ዶት ኮም - ቴክኖሎጂ ለቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • አገልግሎቶች
    • የማማከር አገልግሎት
    • የአጥቢያ አስተዳደር መተግበሪያ
  • ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

በስዊዘርላንድ ለሚገኙ የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል አገልጋዮች የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተሰጠ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ ፀሐየ ጽድቅ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ጄኔቫ የአዳጊ ወጣቶች መንፈሳዊ ትምህርት ቤት አስተባባሪነት በስዊዘርላንድ ለሚገኙ የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል አገልጋዮች በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰጠው የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. (ማርች 31፣2026) ተጠናቋል።

ስልጠናው በ 6 መርሐግብሮች የተሰጠ ሲሆን የተሸፈኑት ዋና ዋና አርእስት የለውጥ አመራር፣ ኦርቶዶክሳዊ ሥራ አመራር፣ የሥራ መመሪያ፣ ውጤታማ ተግባቦት እና ውጤታማ ስብሰባ፣ እቅድ፣ ትግበራ፣ ክትትል እና ግምገማ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ አመራር እንደሆኑ ተገልጿል። ስልጠናው በገለጻ፣ በውይይት፣ መነሻ ሰነዶችን በማቅረብ እንዲሁም በተግባራዊ እንቅስቃሴ (የቤት ሥራ) የታገዘ አፈጻጸም የነበረው ሲሆን ይህም ተሳታፊዎች የሚቀርብላቸውን መነሻ ይዘት ለመተግበር እና በግላቸው በጥልቀት ለመከታተል እድል የሰጠ ሆኗል።

የስልጠናው አስተባባሪ ፀሐየ ጽድቅ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን ጄኔቫ የአዳጊ ወጣቶች መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ከስልጠናው የተገኙ መነሳሳቶችን እና ጅማሮዎችን በሕብረት እና በመናበብ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ያሳወቀ ሲሆን ስልጠናውን የሰጠውን አጥቢያ ዶት ኮምን አመስግነዋል። በቀጣይም የአተገባበር ክትትል እና እገዛ እንዳይለያቸው አደራ በማለት መርሐግብሩ ፍጻሜን አግኝቷል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/Screenshot-from-2026-04-01-22-21-50-cover.png 400 400 tc https://atbiya.com/a/wp-content/uploads/atbiya.com-am-slogan.png tc2026-04-01 20:18:562026-04-01 20:41:21በስዊዘርላንድ ለሚገኙ የሕጻናት እና አዳጊዎች ክፍል አገልጋዮች የውጤታማ ሥራ አመራር ስልጠና ተሰጠ

በፌስቡክ ያግኙን

© አጥቢያ ዶት ኮም
  • Link to Facebook
Link to: የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ድረ ገጽ ተለቀቀ Link to: የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ድረ ገጽ ተለቀቀ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ድረ... Link to: በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃማኖት ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክሳዊ ሥራ አመራር እና ተግባቦት ስልጠና ተሰጠ Link to: በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃማኖት ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክሳዊ ሥራ አመራር እና ተግባቦት ስልጠና ተሰጠ በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃማኖት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top