የስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ድረገጽ ተሻሽሎ ቀረበ

ታኅሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም.
+ + +

የስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ድረገጽ ተሻሽሎ ቀረበ። ድረገጹ ከዚህ ቀደም በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ ሲሆን የዶሜይን ስም እና የገጽታ ለውጥ በማድረጉ በአዲስ መልኩ እንዲሻሻል ምክንያት መሆኑ ታውቋል

 

 

የኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛወረ

ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም.
+ + +
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የሚገኘው ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከዚህ ቀደም በፈቃደኛ አገልጋዮች ሲያስተዳደር የነበረውን የድረገጽ እና ተያያዥ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ወደ አጥቢያ ዶት ኮም አዛውሯል። የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ተስፋሚካኤል መኮንን ይህንን ለማድረግ ያስፈለገው በሁለት ዋና ምክንያቶች እንደሆነ ገልጸዋል። እነሱም፦
  1. ድረገጹን ሲያስተዳደሩ የነበሩ ፈቃደኛ አገልጋዮች ባጋጠማቸው የስራ ጫና እና ተያያዥ ምክንያቶች ድረገጹ የሚያስፈልገውን የእለት ተእለት ክትትል ለማድረግ ባለመቻሉ እና የአገልግሎት መቋረጥ በማጋጠሙ እና
  2. በቀጣይ ከድረገጽ ባለፈ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ እና የማዘመን ስልታዊ አቅጣጫን ደብሩ በማስቀመጡ ነው ብለዋል።
አጥቢያ ዶት ኮም የደብሩን ድረገጽ በጥንቃቄ በነበረበት መልኩ ያለምንም የአገልግሎት መቋረጥ (zero downtime) ወደ አጥቢያ ዶት ኮም ሰርቨሮች ያሸጋገረ ሲሆን በቀጣይ የገጽታ እና ሌሎች ማሻሻያዎችን በማድረግ የድረገጹን ተደራሽነት ለማሳደግ ስራዎችን እንደሚሰራ ታውቋል።

ፎቶ፦ ቀሲስ ተስፋ ሚካኤል መኮንን

የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት የተሰራው የዚህ አመት (2015) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በፕሮጀክቱ ሒደት ልዩ ልዩ የሲስተም ማሻሻያ ስራዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የተካሔዱ ሲሆን የዚህ አመት ዲጅታል መጽሔት በይዘት እና በጥራት ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑ ታውቋል። ዲጅታል የምረቃ መጽሔቱ ለተመራቂዎች ከዛሬ ጀምሮ በስርጭት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያው የማስተዋወቂያ መርሐግብር እንደሚያዘጋጅ ታውቋል።።

አጥቢያ ዶት ኮም ለፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት አስተባባሪዎች (በሁሉም እርከን ላይ የሚገኙ) ከፍ ያለ ምስጋናን ያቀርባል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ድረ-ገጽ ተለቀቀ

የሀገረ ስብከቱ ድረገጽ በብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ ቡራኬ ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ስራ ጀምሯል።

ድረገጹ የሀገረ ስብከቱን መሠረታዊ መረጃዎች፣ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎች ስልታዊ ይዘቶችን ለህዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ታልሞ የተሰራ እንደሆነ ታውቋል። ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ በማሳያ መርሐግብሩ ላይ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የባለሞያዎች አስተዋጽዖ ወሳኝ እንደሆነ አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል።

የሀገረ ስብከቱን ድረገጽ ይመልከቱ

የማኅበረ ቅዱሳን የ2015 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጀመረ

አጥቢያ ዶት ኮም የዚህን ዓመት /2015 ዓ.ም./ የማኅበረ ቅዱሳን ግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ዝግጅት ስራን ጀምሯል።

የትግበራ ፕሮጀክቱ በ2 ግብረ ኃይሎች የተከፈለ ሲሆን በትግበራው ግዜ ሰሌዳ መሰረትም ፕሮጀከቱ ሰኔ 30 ላይ ይጠናቀቃል። ፕሮጀክቱ የተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ ማስገባት፣ ዲጅታል መጽሔቱን የማዘጋጀት እና ተደራሽ የማድረግ ዋና ዋና ግቦችን ይዞ የሚሰራ ይሆናል።

አጥቢያ ዶት ኮም ባለፈው የትምህርት ዘመን (2014 ዓ.ም.) በተመሳሳይ ትግበራ የተመራቂዎችን መጽሔት በጥራት እና በተፈለገው የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ እና ተደራሽ ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ይፋዊ ድረ-ገጽ ተለቀቀ !

በአጥቢያ ዶት ኮም የተስራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ይፋዊ ድረገጽ የ2015 ዓ.ም. ጥምቅት በዓልን ምክንያት በማድረግ ተለቀቀ።

ድረገጹ በቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ማኅበራዊና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሕዝበ ክርስታያኑ በቴክኖሎጂ የታገዙ መረጃዎችን ማግኘት ይችል ዘንድ ሥራውን እንዲጀምር አድርጓል። በቀጣይም ድረገጹ በይዘት እየጎለበተ እንደሚሄድ እና መሰረታዊ፣ ወቅታዊ እንዲሁም ስልታዊነት ያላቸው መረጃዎ የሚለቀቁበት ዋናው ገጽ እንደሚሆን ታውቋል።

የድረገጽ አስተዳደር ሥልጠና ተሰጠ

አጥቢያ ዶት ኮም በቅርቡ ሰርቶ ያስረከበውን የስዊድን፣ ስካንዲናቭያና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ድረገጽ የማስተዳደር ሥልጠና ሀገረ ስብከቱ የአይ.ሲ.ቲ. /Information Communication Technology/ ክፍል አባላት ትናንት ኅዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ተሰጠ።

በሥልጠናው የአይ.ሲ.ቲ. ክፍሉ በአጥቢያ ዶት ኮም አጋዥነት ያዘጋጀው የድረገጽ አስተዳደር መመሪያ ላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን ድረገጹ ስለሚመራበት የተለያዩ የትግበራ ሂደቶች ውይይት ተደርጓል። በቀጣይም የድረገጹ መተግበሪያ ዝርዝር ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ከባለሞያዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል። በመርሐግብሩ ሁለት ካህናት አባቶች በመገኘት መርሐግብሩን የባረኩ ሲሆን ጥሩ ጅማሮ መሆኑን እና ከዚህም በላይ መስራት እንደሚገባ በመግለጽ የማበረታቻ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ የስዊድን እና ስካንዲናቭያ ሀገሮች አህጉረ ስብከት ድረገጽ ተለቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም አበልጻጊነት የተሰራው የአህጉረ ስብከቱ ድረገጽ የመነሻ መረጃዎችን በመያዝ በመስቀል እለት መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ ውሏል። በቀጣይ ድረገጹ  ልዩ ልዩ መሰረታዊ፣ ወቅታዊ እና ስልታዊ ይዘቶች  የሚለቀቁበት ሲሆን አህጉረ ስብከቱን የበለጠ ተደራሽ እንደሚያደርገው ታውቋል።

ለፕሮጀከቱ መሳካት አስተዋጽዖ ላደረጉ በሙሉ በሙሉ አጥቢያ ዶት ኮም ከፍ ያለ ምስጋና ታቀርባለች።

ድረገጹን በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ

በኤ/ኦ/ተ/ቤ የስካንዲናቭያ እና ፊንላንድ ሀገረስብከት ድረገጽ ተሻሽሎ ተለቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም አበልጻጊነት የተሰራው የሀገረስብከቱ ድረገጽ ትልቅ የሆነ የቴክኖሎጂ እና የገጽታ ማሻሻል ተደርጎበት ክለሳ 3 (version 3) ለተጠቃሚዎች ቀርቧል። በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቢተክርስትያን የስካንዲናቭያ እና ፊንላንድ ሀገረስብከት ድረገጽ ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ. በ2014 ዓ.ም. የተሰራ ሲሆን ሁለተኛ ማሻሻያ በ2019 እንደተደረገለት ታውቋል።

ከቴክኖሎጂ ተለዋዋጭነት አንጻር አጥቢያ ዶት ኮም ድረገጹን የማሻሻል እና የማዘመን ስራዎችን በየጊዜው እየሰራ መሔዱ ሁሌም እንደሚያስደስታቸው ሊቀ ካህናት ቀሲስ አፈወርቂ ተስፋ ገልጸዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን የ2014 ዓ.ም. ግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ ተጠናቀቀ

በአጥቢያ ዶት ኮም ፕሮጀክት ተቋራጭነት ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጀመረው የዚህ አመት (2014) የግቢ ጉባኤያት ተመራቂዎች ዲጅታል መጽሔት ስራ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጠናቀቀ። በፕሮጀክቱ ሒደት ልዩ ልዩ የሲስተም ማሻሻያ ስራዎች፣ ስልጠናዎች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች የተካሔዱ ሲሆን የዚህ አመት ዲጅታል መጽሔት በይዘት እና በጥራት ደረጃው ከፍ ያለ መሆኑ ታውቋል። ዲጅታል የምረቃ መጽሔቱ ለተመራቂዎች ከዛሬ ጀምሮ በስርጭት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይም የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያው ሙሉ የትግበራ አቅጣጫውን በተዘጋጀው መተግበሪያ እንደሚያደርግ ታውቋል።

አጥቢያ ዶት ኮም ለፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት አስተባባሪዎች (በሁሉም እርከን ላይ የሚገኙ) ከፍ ያለ ምስጋናን ያቀርባል።